የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማደራጀት ባወጣዉ አዋጅ ቁጥር 84/2016 ዓ.ም መሰረት ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሚሰጡ 3 ተጠሪ ተቋማት የጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት፣ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት እና የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እንዲሁም በውክልና ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጨማሪም የወረዳ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤቶችን የመምራት፣ የመደገፍ፣ የማስተባበርና የመቆጣጠር ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡
የልደታ ክፍለ ከተማ ሥራ አስከያጅ ጽ/ቤት በስሩ የተደራጁ ተጠሪ ተቋማትን እና የወረዳ ሥራ አሰኪያጅ ጽ/ቤቶችን በማስተባበር በ2018 በጀት ዓመት ከዝግጅት እስከ ትግበራ ምዕራፍ ያሉ ቁልፍ እና አበይት ስራዎችን በተገቢው ሁኔታ በማከናወን እንዲሁም የተቋማዊ ሪፎርም ስራዎችን በልዩ ትኩረት ተግባራዊ እንዲደረጉ በመደገፍ፣ ከተቋማትና ባለድርሻ አካላትን በማቀናጅት እና በማሳተፍ የማዘጋጃ ቤታዊ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሳለጥ የማድረግ፣ የተቋማት አፈጻጸም ክትትል እና ድጋፍ የማድረግ፣ ለዘርፉና ባለድርሻ አካላት ክፍተትን መሰረት ያደረገ ስልጠና በመስጠት የመፈጸም እና ማስፈጸም አቅም የመገንባት፣ ክፍለ ከተማችን ፅዱና ውብ የስራና የመኖሪያ አካባቢ የማድረግ፣ ቀልጣፋና በቴክኖሎጂ የተጋዘ የኩነትና የነዋሪነት አገልግሎት እንዲሰጥ የማድረግ እና የእሳትና ሌሎች የአደጋዎች እንዳይከሰቱ ቅድሚያ የመከላከል እንዲሁም ... ተጨማሪ ያንብቡ
አቶ ያየህ አለም , የልደታ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ