የልደታ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 84/2016 መሰረት የሚከተሉት ስልጣንና ኃላፊነት ይኖሩታል

  1. ተጠሪነታቸው ለእርሱ የሆኑ አስፈጻሚ አካላትን በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤ ይቆጣጠራል፤
  2. ዕቅድና በጀት ከከተማው ስራ አስኪያጅ ጋር በመመካከር በማዘጋጀት ለክፍለ ከተማው ዋና ሰራ አስፈፃሚ ያቀርባል፣ሲፀድቅም ተግባራዊ መሆኑን ያረጋግጣል
  3. የስራ አፈፃፀም ሪፖርቱን አዘጋጀቶ ለከተማው ስራ አስኪያጅና ለክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ያቀርባል
  4. በቻርተሩ የተሰጡትን ሌሎች ሥልጣንና ተግባራት እንዲሁም በክፍለ ከተማው የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል
  5. ለክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በተጨማሪ እንዲሰራቸው በአዋጅ ቁጥር 74/2014 ዓ.ም እንዲካተቱ ታሳቢ የተደረጉ ስልጣንና ተግባራትን ያከናውናል