የልደታ አስተዳደር ህንጻ 7ኛ ወለል ቢሮ ቁ 702
+251946086645
የቅሬታ አስተያየት መስጫ
ዓርብ, ህዳር 14, 2016 ዓ.ም
መግቢያ
ስለ እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
ተቋማዊ አደረጃጀት
የጽ/ቤቱ ቡድን መሪና ባለሙያዎች
የደንበኞች አገልግሎት
አገልግሎቶች
የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት
የቅሬታ አስተያየት መስጫ
የአገልግሎት እርካታ አስተያየት መስጫ
የጽ/ቤቱን ሮቦት ይጠይቁ
ሚዲያ
ዜና | News
ዶክመንተሪ (ቲቪ)
Video News
መጽሄት | Magazine
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
የዶ/ር ዐቢይ መጽሀፍቶች
ብሮሸር | Brochure
በራሪ ወረቀት
ማስታወቂያ
ይግቡ
መግቢያ
ስለ እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
የዜጎች የስምምነት ሰነድ
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ሚዲያ
ዜናዎች | News
መጽሄቶች | Magazine
Online TV
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
Web APP
ይግቡ
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከተማ የ2 ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የጂ+4 ማስፋፊያ ግንባታ ማስጀመሪያ ተካሄደ
ታህሳስ 22, 2018
በክ/ከተማው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የፍሬህይወት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የጂ+4 የማስፋፊያ ግንባታ ማስጀመሪያ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በማስፋፊያ ግንባታው ማስጀመሪያ ወቅት እንደተናገሩት ከተማችን አዲስ አበባን ህፃናትን ለማሳደግ ምቹ ከተማ እናደርጋለን የሚለውን የክብርቲ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ኢንሼቲቭ ወስደን በትምህርቱ ዘርፍ በመተግበር እና ትውልድ ግንባታ ላይ ትኩረት አድርገን በመስራት አበረታች ውጤት አስመዝግበናል ሲሉ ገልፀዋል። የማስፋፊያ ግንባታው የትምህርት ተደራሽነትን፣ ጥራትን እና ደረጃን በማሻሻል የመማር ማስተማር ስራን ለማሳለጥ እየሰራነው ላለው ተግባር አጋዥ ይሆናል ያሉ ዶ/ር ዘላለም ግንባታው በአጠረ ጊዜ ተጠናቆ ወደ ተግባር እንዲገባም በቅንጅት ይሰራል ትምህርት ቢሮም ክትትል ያደርጋል በማለት ገልፀዋል። ለትውልድና ለሀገር ግንባታ ቅድሚያ ሰጥቶ ይህንን የማስፋፊያ ግንባታ ወደ ተግባር ላስገባ የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደርም በት/ቢሮ ስም እናመሰግናለን በማለት ገልፀዋል ዶ/ር ዘላለም። የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደተናገሩት ዛሬ ያስጀመርነው የማስፋፊያ ግንባታ በመምህራን፣ በወላጆችና በተማሪዎች ዘንድ ለረጅም ዓመታት የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ ሲነሳ የነበረ ነው ብለው አስተዳደሩም ይህንን የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ ግንባታውን አስጀምሯል ሲሉ ገልፀዋል። የማስፋፊያ ግንባታው የትምህርት ስርዓቱን ለማሻሻል እየተሰሩ ላሉ ተግባራት ተደማሪ አቅም ይሆናል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተቋማትን በአሰራር እና በአደረጃጀት እንዲዘምኑ በማድረግ በእውቀትና በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድን ለመፍጠር በትጋት እንሰራለን በማለት ገልፀዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም መንግስት ከለውጡ በፊት በትምህርት ዘርፉ በየነበሩ ስብራቶችን በመጠገን በእውቀት የዳበረ ተመራማሪ የሆነ ሀገርን የሚረከብ ትውልድ ለመገንባት እየሰራ ነው ብለው እንደ ልደታም ተግባሩን ስኬታማ ለማድረግ በትኩረት እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ዜና | Oduu | News
የመሠረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ፈጣን፣ ቀልጣፋና ግልፀኝነት የተላበሱ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸው ተገለፀ።
ታህሳስ 21, 2018
በልደታ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እና ተጠሪ ተቋማት እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶች ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ግልፀኝነት የተላበሱ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ገለፀ። ከአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እና ተጠሪ ተቋማት የተውጣጣ የምልከታ ቡድን በልደታ ክ/ከተማ ለተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የነበረው የመሠረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የስራ እንቅስቃሴ በመስክ ምልከታ ያሉበት ደረጃ ተወዋውሮ የተመለከተ ሲሆን የግኝቱ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። የምልከታ ቡድኑን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ አማካሪ አቶ ይብሬ ኢስማኤል ሲሆኑ ባካሄድነው የመስክ ምልከታ በተቋማቱ የነዋሪውን የመልካም አስተዳደር ችግር ፈቺ የሆኑ ተግባራት መከናወኑን ተገንዝበናል ብለዋል። አቶ ይብሬ አክለዉም በተቋማቱ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱ በቴክኖሎጅ መዘመኑ፣ ሥራዎችን ከሌሎች ተቋማት ጋር ተናባቢ በሆነ መልኩና ቅንጅታዊ አሠራርን ባጠናከረ መልኩ በመፈጸሙ እምርታዊ ለዉጥ ማምጣት የተቻለበት ስራ መሠራቱን ገልፀዋል። በክ/ከተማው የሚገኙ የመሠረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ስሉጥ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት በማረጋገጥ ረገድ የመጣዉን ለዉጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አቶ ይብሬ አሳስበዋል። በዚሁ መድረክ ላይ በሁሉም ተጠሪ ተቋማቶች ሰፋፊ ስራዎች የተከናወኑበት መሆኑ የተገልፀ ሲሆን በተለይም ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ከህብረተሰቡ የሚነሱ ቅሬታዎችን መፍታት የቻልንበት፣ የሚሰጡ አገልግሎቶች በይበልጥ ከቴክኖሎጂ ጋር ተሳስረው ማዘመን የቻልንበትና በዚህም እምርታዊ ለውጥ የመጣበት መሆኑ ተመላክቷል። የክ/ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤቱ እና ተጠሪ በሆኑት የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት፣ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ቅርንጫፍ፣ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር፣ በፅዳት አስተዳደርና በአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አገልግሎት አሰጣጥና ሌሎች የስራ እንቅስቃሴዎች ላይ ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ምልከታ መደረጉ ከመድረኩ መረዳት ተችሏል።
ዜና | Oduu | News
ቆሻሻን በተገቢው መንገድ በማስወገድ ምቹ የመኖሪያ አካባቢ እንዲፈጠር እየሰራ መሆኑን የልደታ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ገለጸ።
ጥቅምት 24, 2018
ጽ/ቤቱ ከተማ አቀፍ በማሆበረሰቡ የደረቅ ቆሻሻ ከምንጩ የመለየት ንቅናቄ ማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሄደ። በፕሮግራሙ ላይ የጽዳት አምባሳደሮች፣ባለሙያዎች፣የሽርክና ማህበራት፣ ነዋሪዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። በፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የልደታ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያየ ዓለም እንደገለጹት የደረቅ ቆሻሻ አያያዝን በማስተካከልና ከምንጩ በመለየት በቅብብሎሽ በማጓጓዝ የሚፈለገው ቦታ በማድረስ አካባቢያችንን በንጽህና በመያዝ ለመኖሪያ ምቹ እንድትሆን በመተባበር ልንሰራ የሚገባ መሆኑን ገልጸዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሓዱሽ ሓጎስ በበኩላቸው የንቅናቄው ዓላማ ቆሻሻን በተገቢው መንገድ የሚበሰብሱ ቆሻሻዎችንና የማይበሰብሱትን ከምንጩ በመለየት ጥቅማ ላይ እንዲውል ለማድረግና ደረቅ ቆሻሻ ከሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ መልሶ ጥቅም ላይ እንዲዉሉ ለማድረግ መሆኑን ተናግረዋል። ደረቅ ቆሻሻን መልሶ ኡደት በማድረግ ይሰጠው ከነበረው አገልግሎት በሙሉ ወይም በከፊል ለሌላ አገልግሎት ማዋል በትኩረት ከተሰራበት የሀብት ምንጭ መሆኑን የገለጹት አቶ ኃዱሽ ደረቅ ቆሻሻን ጥቅም ላይ ለማዋል በሚከናወነው ተግባር የተደራጁ የሽርክና ማህበራት፣ባለሙያዎች፣የጽዳት አምባሳደሮችና ህብረተሰቡ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ደረቅ ቆሻሻን ከምንጩ በመለየት መልሶ የመጠቀም ባህልን ልናሳድግ ይገባል ብለዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት አዲስ አበባ ከተማን ገጽታ የቀየሩ በርካታ የልማት ስራዎች መሠራታቸውን ገልጸው ቆሻሻን በየቦታው ከመጣል ተቆጥበን ቆሻሻን በአግባቡ በመለየትና መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል አካባቢያችን ለመኖሪያ ምቹ የተጀመሩ የልማት ስራዎችም ቀጣይ እንዲሆኑ መስራት የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን ተናግረዋል።
ዜና | Oduu | News
የፅዳት ዘመቻውን የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤትና ከወጣት ማህበር ጋር በመተባበር ነው ያካሄዱት።
ጥቅምት 24, 2018
በልደታ ክ/ከተማ የፅዳት ዘመቻ ተከናወነ የዘመቻው ዓላማ ውብ ፅዱና አረንጓዴ አካባቢን በመፍጠር ሂደት ወጣቶች ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑን ተገልጿል።
ዜና | Oduu | News
ሙስናን እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በቅንጅት መታገል እንደሚገባ ተገለፀ።
ህዳር 11, 2018
ስልጠናውን የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከክ/ከተማ ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና መከታተያ ክፍል ጋር በመተባበር ተሰጥቷል በመድረኩ የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች የጽዳት አምባሳደር ታዋቂ አርቲስቶች እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተገኝተዋል ተካፍለዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ያየህ አለም እንዳሉት የሥነ ምግባር ጉድለትና ሙስናና ብልሹ አሰራር የሚፀየፍና የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋ ለመፍጠር በሚደረገው የፀረ ሙስና ትግል ላይ የራሱን ሀላፊነት በመወጣት እንዳለበት ገልፀዋል የስልጠና ተሳታፊዎችም ስልጠናው የተሻለ መሆኑን በመግለፅ በሚደረገው የፀረ ሙስና ትግል ላይ ሁሉም የራሱን ሀላፊነት መወጣት አለበት በማለት አንስተዋል።
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክፍለ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የመልካም አስተዳደርና ቅሬታ አፈታትን አፈፃፀም ገመገመ።
ህዳር 1, 2018
የልደታ የልደታ ክፍለ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸምን ከወረዳ አመራሮች ቡድን መሪዋችና ባለሞያዋች ጋር ገምግሟል። በሩብ ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት በቅንጅት የተሰሩና ጥሩ ውጤት የተመዘገበባቸው ናቸው ብለው ይህ ተግባር እንዲሳካም ሲሰሩ ለነበሩ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል። የክ/ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያየህ ዓለም በክፍለ ከተማዉ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት እየተሰሩ ያሉ ስራዋች አበረታችና ችግር ፈቺ መሆናቸዉን ገልፀዉ በቀጣይ ተጠናክረዉ መቀጠል እንዳለባቸዉ ገልፀዋል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ መቅደስ ያደታ በበኩላቸው የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም የተሻ እንደተፈፀመና በቀጣይ ግን አገልግሎት አሰጣጡን ለማለቅ እንዲቻል ተከታታይነት ያለዉ ስራ መሰራት እንዳለበት አስቀምጠዋል :: የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በሩብ ዓመቱ ስኬታማ ስራ ተሰርቷል ያሉ ሲሆን በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከተማ "ሳምንታዊ "የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።
ጥቅምት 24, 2018
በዘመቻው የክ/ከተማው አፈ ጉባኤ አቶ ዘሪሁን ሺፈርዳ /የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ጢቂ ድሪባ ፣የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ተወካይ አቶ እንግዳው ጋዴ፣አርቲስቶች ፣የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈውበታል። የልደታ ክ/ከተማ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ዘሪሁን ሺፈርዳ በዘመቻው ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ፅዳት የአንድ ተቋም ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ህብረተሰብ ቅንጅታዊ ተግባር ነው ብለው ማህበረሰቡ ፅዳትን ባህሉ በማድረግ ለኑሮ ምቹና ተስማሚ አዲስ አበባን መፍጠር ይኖርበታል ብለዋል። አቶ ዘሪሁን አክለውም ብሎክ ሲፀዳ በድምር ውጤት ወረዳ ይፀዳል፤ ወረዳ ሲፀዳ ክ/ከተማ ሁሉም ክ/ከተሞች ሲፀዱ ደግሞ ከተማችን ውብ ትሆናለች ብለዋል። የክ/ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያየህ ዓለም በበኩላቸው ሁላችንም ለአካባቢ ፅዳት ትኩረት በመስጠት ከተማችንን ውብና ማራኪ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል። አካባቢያችንን ዘወትር በማፅዳት ውብ፣ ፅዱና ምቹ የሆነ የመኖሪያ አካባቢን መፍጠር ይኖርብናል ብለዋል። አቶ ያየህ አክለውም አዲስ አበባን እንደ ስሟ ንፁህና ፅዱ እናደርጋለን ለዚህም ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት፥ ህብረተሰቡ ዘውትር አከባቢውን ማፅዳትና ቆሻሻን በተገቢው ቦታ ማከማቸት እንደሚኖርበት ተናግረዋል #ፅዳት የዘመናዊነት መገለጫ ነው!! #ዘውትር አከባቢያችን በማፅዳት ፅዱ፣ ውብና ለመኖሪያ ምቹ የሆነ ስፍራን እንፍጠር!!
መግቢያ
ስለ_እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ሚዲያ
ዜናዎች | News
ፎቶግራፎች | Photo Gallery
ቪዲዮዎች | Videos
መግለጫዎች | Press Release
መጽሄቶች | Magazine
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
Online TV
Web APP
ያግኙን
lidetamanager@gmail.com
+251946086645