Welcome to Lideta Subcity Manager Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የብልጽግና ተምሳሌት ሆና ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፍ አሰራርን በመተገበርና አገልግሎቱን በማዘመን ውጤታማ ስራዎች መሰራቱ ተገለፀ ፡፡

ጥቅምት 4, 2018
የልደታ የልደታ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ማዘጋጃ ቤታዊ ስራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ። ጽ/ቤት በተጠሪ ተቋማት የተከናወኑ የ1ኛ ሩብ ዓመት ስራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል። የልደታ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ደረጄ ተሪቦ እንደገለፁት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ላይ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን በርካታ የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መቻሉን ገልፀዋል ። የከተማውን የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን በማዘመንና በጥራት በመስጠት የተገኘውን ውጤት ማስቀጠል ይገባል ያሉት አቶ ደረጄ አያይዘው ቀጣይም የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን ለማከናወን እንደሚያስችልም ጠቅሰዋል። በወቅቱ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቱ እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቶ ደረጄ ተሪቦ ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ያየ ዓለም በክፍለ ከተማው የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተቀላጠፈ ውጤታማና ዘመናዊ አሰራር በመዘርጋት የከተማውን የክ/ከተማውን ዕድገት በሚመጥን መንገድ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል። ስራዎችን በቅንጅትና በቁርጠኝተነት በተዋረድ በመስራት እየመጣ ያለውን ውጤት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል። በክፍለ ከተማው ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ በማዘመን በተቀላጠፈ አሰራር ዘርፈ ብዙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመቅረፍን የገለፁት አቶ ያያ አያይዘው በተቀናጀ አግባብ ተግባራትን መፈፀም እንደሚገባ ገልፀዋል። የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዘመድኩን በቀለ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በተቀላጠፈና በተቀናጀ ተግባራት በመፈፀም የተሻለ ውጤት እየመጣ እንደሆነ ገልፀዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎችም በፅዳት ዙሪያ ከተማውን ውብና ፅዱ ከማድረግ አንፃር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አጠናክረን መስራት ይገባል ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች