Welcome to Lideta Subcity Manager Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የብልጽግና ተምሳሌት ሆና ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ "ሳምንታዊ "የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።

ጥቅምት 24, 2018
በዘመቻው የክ/ከተማው አፈ ጉባኤ አቶ ዘሪሁን ሺፈርዳ /የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ጢቂ ድሪባ ፣የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ተወካይ አቶ እንግዳው ጋዴ፣አርቲስቶች ፣የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈውበታል። የልደታ ክ/ከተማ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ዘሪሁን ሺፈርዳ በዘመቻው ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ፅዳት የአንድ ተቋም ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ህብረተሰብ ቅንጅታዊ ተግባር ነው ብለው ማህበረሰቡ ፅዳትን ባህሉ በማድረግ ለኑሮ ምቹና ተስማሚ አዲስ አበባን መፍጠር ይኖርበታል ብለዋል። አቶ ዘሪሁን አክለውም ብሎክ ሲፀዳ በድምር ውጤት ወረዳ ይፀዳል፤ ወረዳ ሲፀዳ ክ/ከተማ ሁሉም ክ/ከተሞች ሲፀዱ ደግሞ ከተማችን ውብ ትሆናለች ብለዋል። የክ/ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያየህ ዓለም በበኩላቸው ሁላችንም ለአካባቢ ፅዳት ትኩረት በመስጠት ከተማችንን ውብና ማራኪ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል። አካባቢያችንን ዘወትር በማፅዳት ውብ፣ ፅዱና ምቹ የሆነ የመኖሪያ አካባቢን መፍጠር ይኖርብናል ብለዋል። አቶ ያየህ አክለውም አዲስ አበባን እንደ ስሟ ንፁህና ፅዱ እናደርጋለን ለዚህም ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት፥ ህብረተሰቡ ዘውትር አከባቢውን ማፅዳትና ቆሻሻን በተገቢው ቦታ ማከማቸት እንደሚኖርበት ተናግረዋል #ፅዳት የዘመናዊነት መገለጫ ነው!! #ዘውትር አከባቢያችን በማፅዳት ፅዱ፣ ውብና ለመኖሪያ ምቹ የሆነ ስፍራን እንፍጠር!!

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች