Welcome to Lideta Subcity Manager Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የብልጽግና ተምሳሌት ሆና ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የመልካም አስተዳደርና ቅሬታ አፈታትን አፈፃፀም ገመገመ።

ጥቅምት 28, 2018
የልደታ የልደታ ክፍለ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸምን ከወረዳ አመራሮች ቡድን መሪዋችና ባለሞያዋች ጋር ገምግሟል። በሩብ ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት በቅንጅት የተሰሩና ጥሩ ውጤት የተመዘገበባቸው ናቸው ብለው ይህ ተግባር እንዲሳካም ሲሰሩ ለነበሩ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል። የክ/ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያየህ ዓለም በክፍለ ከተማዉ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት እየተሰሩ ያሉ ስራዋች አበረታችና ችግር ፈቺ መሆናቸዉን ገልፀዉ በቀጣይ ተጠናክረዉ መቀጠል እንዳለባቸዉ ገልፀዋል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ መቅደስ ያደታ በበኩላቸው የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም የተሻ እንደተፈፀመና በቀጣይ ግን አገልግሎት አሰጣጡን ለማለቅ እንዲቻል ተከታታይነት ያለዉ ስራ መሰራት እንዳለበት አስቀምጠዋል :: የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በሩብ ዓመቱ ስኬታማ ስራ ተሰርቷል ያሉ ሲሆን በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች