Welcome to Lideta Subcity Manager Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የብልጽግና ተምሳሌት ሆና ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ ከተማ አቀፍ የፅዳት የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ።

ህዳር 20, 2018
በጽዳት ዘመቻው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሰፋ ቶላ እንደተናገሩት ፅዳትን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ እየፈጠርን ከተማችን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት እንድትሆን እየሰራን ነው ብለው በዚህም አበረታች ውጤቶችን አስመዝግበናል በማለት ገልፀዋል። አቶ አሰፋ አክለውም መንግስት የግንዛቤ ስራውን በማጠናከር ፅዳትን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ እንዲፈጠር ከማድረግ ባለፈ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትም እንዲሻሻል ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል ሲሉ ገልፀዋል። ስማርት ሲቲን ለመገንባት የተያዘው ስራ እንዲሳካ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓታችንን የማዘመን ስራ እየተሰራ መሆኑንም አቶ አሰፋ ገልፀዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ደሲሳ እንደተናገሩት ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ፅዱ ውብና ለኑሮ ተስማሚ የሆነች ከተማን ለመፍጠር በትኩረት ተሰርቷል ብለው በዚህም ስኬታማ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል። አቶ ገዛኸኝ አክለውም ፅዳትን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ ለመፍጠር የቤት ለቤት ግንዛቤ ማስጨበጥ ስራም ጭምር ሲሰራ ነበረ ብለው በዚህም ውብ ፅዱና ለኑሮ ተስማሚ ከተማን እየፈጠርን ነው በማለት ተናግረዋል። ማህበረሰቡ ውብና ፅዱ ከተማ ለመፍጠር ፅዳትን ከግቢው መጀመር አለበት ያሉት አቶ ገዛኸኝ ማህበረሰቡ ከፅዳት ባለፈ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓቱንም እንዲያሻሽል ጥሪ አቅርበዋል። የልደታ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያየህ ዓለም እንደተናገሩት ንፁህ አካባቢን ለመፍጠር በትኩረት እየሰራን ነው ብለው በዚህም ቆሻሻን የሚፀየፍ ትውልድ እየገነባን ነው በማለት ገልፀዋል። ፅዳትን ባህሉ ያደረገ ትውልድ ለመፍጠር በትምህርት ተቋማትም የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እየተሰራ መሆኑንም አቶ ያየህ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች