Welcome to Lideta Subcity Manager Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የብልጽግና ተምሳሌት ሆና ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

በራስ አቅም ተረጂነት እና ድህነትን ለመቀነስ እየሰራ መሆኑን የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

ህዳር 11, 2018
በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የተረጂነት እና ድህነት ቅነሳ ተግባራት አፈፃፀም አጠቃላይ አመራር በተገኘበት ተገመገመ። የውይይት መድረኩን የመሩት የልደታ ክ/ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍታለው ከፍያለው ሲሆኑ የልመናና ተረጂነት ቅነሳ የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር ሀገራችን በተያዘው ከተረጂነት ለመላቀቅ የምታደርገውን ጥረት ማሳካት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። አስተዳደሩ በራስ አቅም ተረጂነትን ለመቀነስ እየሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ፍታለው የውጭ ሀገራት እርዳታ የሀገርን ክብር የሚያወርድና ተረጂነት የሚያስፋፋ በመሆኑ መንግስት በእራስ አቅም ተረጂነትን ለመቀነስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በየደረጃው የታዩ የአፈፃፀም ጉድለቶችን በማረም የተመዘገቡ ስኬቶች እንዳይቀዛቀዙ መትጋት እንሚገባም አቶ ፍታለው ጨምረውም ገልፀዋል። የክ/ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ያየ አለም በበኩላቸው ተረጂነት የመፍጠር አቅም እና የመስራት ጉልበትን የሚያዳክም በመሆኑ በልዩ ትኩረት መስራት ይገባናል ብለዋል። በግምገማ መድረኩ ተግባሩ የደረሰበት አሁናዊ ሁኔታ ቀርቦ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች