Welcome to Lideta Subcity Manager Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የብልጽግና ተምሳሌት ሆና ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

በተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ፈጣን ቀልጣፋና ምልልስን ያስቀረ አገልግሎት እየተሰጠ ነው ሲል የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገለፀ።

ህዳር 25, 2018
በክ/ከተማው እየተሰጠ ያለው የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደተናገሩት በአስተዳደሩ በየደረጃው የሚሰጡ አገልግሎቶች ፈጣን ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል በትኩረት እየሰራን ነው ብለው ከምልልስ የፀዳ አገልግሎትን ለማስፈን ተቀናጅተን እየሰራን ነው በማለት ገልፀዋል። በምንሰጠው አገልግሎት የማህበረሰቡን እርካታ በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ እየሰራን ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አገልግሎትን ማሻሻልና ማዘመን የሁሉም የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች መሰረት በመሆኑ በትኩረት እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች